የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ና የ ኣሜሪካ ኣስተያየት ( ባጭሩ)
በኣጭሩ የኣሜሪካ ኣትኩሮት ወይም ኣስተያየት በሚከተሉት ሁለት ኣረፍተ ነገር ዙሪያ የተገነባ ሃሳብ ነው፣
- ግድቡ ለታችኛው ተጠቃሚዎች የውሃ ኣከፋፈል መብት ያከበረ መሆኑን መረጋገጥ ኣለበት፣ እና
- በ ቴክኒክም ለታችኞ ቹ ሃገራት ጉዳት የማያመጣ መሆኑን መረጋገጥ ኣለበት።
እነኚህ ሳይሟሉ ግድቡ መሞላት ወይም አገልግሎት መስጠት ኣይችልም ነው የሚሉት።
እስቲ በሁለተኛው ረድፍ ላይ የተጠቀሰውን እንመርምረው፣ ወይም የሃሳቡን ምንጭ ምን ሊሆን ችላል የሚለዉን እንመልከት ፣
- አባባሉ ግድቡ ቴክኒካልይ ብቁ ላይሆን ይችላል የሚለዉን ሃሳብ ለማስረገጥ የሞከረ ይመስላል። ኢትዮጵያ ግድቡን በራሷ መሃንዲሶች ለመስራት ኣቅም እንደሌላት ኣድርጎ ለማሳየት ና ለማስረገጥ ያሉት የሚመስል እና የሆነ ጉዳት ቢደርስ እንኩዋን፣ እኛም ብለን ነበር ለማለት ያሰቡት ሊሆን ይችላል።
- በሌላ በኩል ስንመለከተው ደሞ፣ በ ኢንፍራ ሬድ (infra red ) ጨረር ከሳተላይት ወይም ከ ሂሊኮፕተር ላይ ግድቡን በማዳከም እንዲፈርስ ካደረጉ በሁዋላ ፣ ምክንያት እንዲሆናቸው ኣስቀድመው እየተዘጋጁም ሊሆን ይችላል.። ማን ያዉቃል፣ ያልጠረጠረ ተመነጠረ ነው ነገሩ።
ቢሆንም ቅሉ ፣ በሁሉም መለኪያ ግድቡ ብቁ ስለመሆኑ ምንም ጥርጣሬ ሊኖር ደሞ ኣይችልም፣ ኣሜሪካዊያን ኢትዮጵያን ቢንቁ እንኩዋን ሳሊኒ ኢምፕረጊሎ (salini impregilo) በግድቡ ስራ ላይ እየተሳተፈ በመሆኑ የነሱን ሃሳብ ዉድቅ ያረገዋል። ስለዚህ፣ ግድቡ በታችኞቹ ሃገራት ጉዳት የማያመጣ መሆኑን ቴክኒካልይ መረጋገጥ ኣለበት ስለማለታቸው ሌላ የተደበቀ ምክንያት ይኖር ይሆናል እንጂ በእዉነት ድክመት ኣለ ብለው ሊያስቡ ኣይቻላቸውም። በተጨማሪም፣ በኢትዮጵያ ዉስጥ የኣባይ ግድብ ለመጀሪያ ግዜ የተሰራ ግድብ ኣይደለም ። ሌሎች ብዙ ግድቦች ቀደም ብሎ ተሰርተዋል ። የኢትዮጵያ ትላልቅ ግድቦች እዚህ ይመልከቱ
በ ጉዳት ማምጣት በኩል ስንመለከተው ደሞ፣ ግድቡ ቢፈርስ እንኩዋን ከግድቡ በ 90 ኪሎሜትር አከባቢ ርቀት ላይ የሱዳን ግድብ Barrage de Roseires, Soudan (Rosereires reservoire) ስላለ ጉዳት የማምጣት ችሎታው ያነሰ ነው ። ጉዳቱ የከፋ ሊሆን አይችልም፣ ምክንያቱም የ Roseires ግድብ መኖር ከላይኛው ተፋሰስ የሚመጣዉን ዉሃ ሃይሉን ሊያበርደው ስለሚችል።
ሌላው የሚገርመው ነገር ግን፣ የአሜሪካም ግድቦች ከብቃት ማነስ የተነሳ የሚፈርሱ መሆናቸው ነው። በኣሜሪካን ሃገር በቴክኒካል ብቃታቸው ጥሩ ሳይሆኑ ቀርተው የፈረሱ ግድቦች እንደምሳሌ የሚከተሉትን መጥቀስ ይቻላል።
Oroville Dam, Colorado Dam disaster
የነሱም ግድብ የሚፈርስ ከሆነ፣ የቴክኒክ ብቃት ስለመናገር የሚችሉ አለመሆናቸውን ያሳያል። ይሄ ማለት ደሞ ፣ ቢራቢሮስ ቂጡዋን ሳትሸፍን ፣ መሬትን መሸፈን ተመኘች ኣሉ ብለው ኣበው እንደሚሉት ይሆንባቸዋል ። ስለዚህ፣ ምክንያታቸው ድብቅ ወይም ሌላ መሆን ኣለበት ያስብላል።
ከላይ በተጠቀሰው ሃሳብ ተመርኩዞ ማለት የሚቻለው፣ በሌላ ሃገር እንደሚያደርጉት ከሳተላይት ወይም ከሂሊኮፕተር በሚላክ ጨረር ግድቡን በማዳከም ማፍረስና ። ከዛም ግድቡ ከብቃት ማነስ ፈረሰ የሚለዉን ለማስረገጥ ያመጡት ሃሳብ ሊሆን ይችላል ወደሚለው ግምታዊ ድምዳሜ ያደርሰናል።
ስለዚህ፣ ይህን ህሳቤ በማሰብ፣ በኢትዮጵያ በኩል ይህ እንዳይመጣ ኣስቀድሞ በግድቡ አከባቢ ምንም አይነት የሂልኮፕተር ወይም የኣይሮፕላን በረራ እንዳይኖር ማገድ ከአደጋው ሊያድን ስለሚያስችል ጥንቃቄ በዚህ በኩልም ቢደረግ ጠቃሚ ወይም ጥሩ ይሆናል ወደሚለው ሃሳብ ያደርሰናል።
ለምሳሌ እንዲሆን፣ ከሂሊኮፕተር ሆነው በጨረር ቤት ሲያፈርሱ የሚያሳየዉን ቪዲዮ ይመልከቱ video 1,
በጣም የሚገርመው ግን ሱዳን Barrage de Roseires, ስትሰራ ለምን ኢጂፕት ኣልተቃወመችም? ለምን ህዳሴ ሲሰራ ተቃወመች ? ይገርማል