ኢትዮጵያ ከዉጭ ሃገራት ለሚገቡ እቃዎች የቀረጥ ኣከፋፈል ስረዓቷን ( ዘይቤዋን) ካላስተካከለች ድህነቷ ይቀጥላል።
አንድ ኢትዮጵያዊ ወጣት ፈጣሪ፣ አስፈላጊ የሚባሉ መሳሪያ ከሌለው እንዴት ለሃገር የሚጠቅም ነገር ሊያፈራ ይችላል። የፈጠራ ስራ እንደ ራእይ ሆኖ ያንን ለማከናወን በቀላሉ መስራት የሚያስችሉ ነገሮች በቅርበት ሊኖሩት ይገባል።
ወደ ሃገር ዉስጥ የሚገቡ ነገሮች፣ በራሳቸው የፈጣሪዉን እዉቀት ያዘሉ በመሆናቸው ። በሃገር ዉስጥ ላለው ፈጣሪ ራዕይን ይፈጥራሉ ለዚህም ነው ዘፋኙ ያላዩትን ሃገር ኣይናፍቁም ሲል የዘፈነው። የልምድ ልዉዉጥ እንደማድረግ ሊቆጠር ይቻላል።
ወደ ሃገር የሚገቡ እቃዎች፣ በተጨማሪም የጥሬ ነገሮችን ኣቅርቦት ያሳድጋሉ ። ለምሳሌ ኣሮጌ መኪና ወደ ሃገር ዉስጥ ቢገባና በሃገር ዉስጥ ቢጣል ። ቢላ ሰሪ እንኩዋን ቢላ መስሪያ ብረት በቀላሉ ሊያገኝ ይችላል። ይሄ ደሞ በሌላ መልኩ በየ ክፍለ ሃገሩ የኤሌክትሪክ ማቆሚያዉን ብረት የሚገነድሱትን ይቀንሳል ማለት ነው ።
እስኪ በሃኪምና በ መሃንዲስ ምሳሌ እንመልከተው
- የልብ ሃኪም ወደ ሃገር ዉስጥ ለማስገባት የሚያስፈልገዉን ማሽን በ 3 እጥፍ ቀረጥ ከከፈለ፣ እንዴት የልብ ሃኪም የሚያስፈልገዉን ማሽን ማስገባት ይችላል። ኣንድ የልብ ሃኪም ማሽን ባስገባ ጊዜ፣
ኣብረዉት የሚሆኑት ነገሮች፣ ማሽኑን የሚሰሩ፣ የሚያንቀሳቅሱ ባለምያተኞች መፈጠራቸዉ ነው፣ ይሄ ደግሞ ስራ ኣጥነትን ይቀንሳል። ስለዚህ በሌላ ሃገር የተመረተ ሆኖ ስራን የሚያቀላጥፍ መሳሪያ ወደ ሃገር ቢገባ ለህዝቦቹዋና ለሃገር ጥቅም እንጂ ጉዳት እንኩዋን የለውም። እንዲያዉም የህክምና ቱሪዝም ማስፋፊያ በሆነች ነበር፣ ሌሎች የኣፍሪካ ሃገሮች በሽተኞችን ባስተናገደች ነበር፣ ይሄ የኣገሪቱን ችግር ከመቅረፉ ባሻገር ፣ የሃገሪቱዋን ሃብትም ይጨምረዋል ፣ ስለዚህ ቀረጥን ማብዛት ሃገሪቱዋን ያደኸያል እንጂ አያሳድጋትም። ቀረጥን ማብዛት በ ግርጅፉ ሲታይ መንግስትን የሚጠቅም ይመስላል ፣ ነገር ግን ሃገር እንዳታድግ ደሞ ማነቆ ሆኖ ይይዛል። ሃገር ቢያድግ ደሞ መንግስትም ቀረጥ መሰብሰብም ባላስፈለገው ነበር። ኣገር እንደ ነ ሳውዲ ኣረቢያ ሆንች ማለት ነው። ለ አንድ ሃገር ቀረጥ መኖር ግዴታም ኣይደለም፣ ነገር ግ ን የቀረጥ አሰራሩ ዘዴ በግዴታ እንዲቀጥል የሚፈለግ ይመስላል። - ኣንድ መሃንዲስ ለስራው ከሚያስገባው መሳሪያዎች በ እጥፍ ቀረጥ ከከፈለ እንዴት ብሎ የሚጠቅመዉን መሳሪያ ያስገባል። ስለዚህ ቀረጥ ቀላልና ምክንያታዊ ሊሆን ይገባል ማለት ነው ። ኣለበለዚያ ቀረጥን አብዝቶ እቃ ወደ ሃገር እንዳይገባ ማድረግ ፣ ኣገሪቱዋን እንዳታድግ ከማድረግ በስተቀረ ሌላ ፋይዳ የለዉም።
በ ኣዉሮፓ ሃገራት ከአፍሪካ ለሚመጡ እዝርዕት፣ (cereals) ከ ቀረጥ ነጻ ያስገባሉ። ምክንያታቸው ደሞ አፍሪካዊያንን ለማገዝ ነው ይላሉ። ሌላ የአፍሪካ ዉጤቶችን (products) ግን ይቀረጣሉ ማለት ነው። በዚህ ምክንያት ደሞ የሚበሉ ነገሮች በሃገራቸው በጣም ርካሽ እንዲሆኑ ያደርጋሉ፣ ኑሮ በዘዴ ነው ይሉሃል ይሄ ነው፣። በ ዘዴ የሌላ ሃገር ሃብት ወደ ሃገራቸው እንዲፈስ ይደረጋል ማለት ነው።
በአገራችን ስንዴ እንኩዋን ወደ ሃገር የሚያስገባ ነጋዴ በ ሁለት እጥፍ እና በ ሶስት እጥፍ ይቀረጣል። ከዛ መንግስት ረሃብ ገባ ፣ የስንዴ ዘር ያስፈልገናል እየተባለ ነጋሪት ይመታል። ይገርማል መተጣጠፍ ባለመቻላቸው የሚጠቅመዉን እንኩዋን ወደ ሃገር ማስገባት ኣይችሉም። ከነሱ ብሶ ኣጎምብሶ እንደሚባለው በተለያየ እቃ ላይ በ 2 ና ብ3 እጥፍ ቀረጥ እያስከፈሉ እቃው ብቻ ሳይሆን በ እቃው ላይ ያለዉን የፈጣሪዉን ስራ እዉቀት ወደ ሃገር እንዳይገባ በማድረግ ሃገሪቱዋን ላደጉ ሃገሮች ሲሳይ እና መመኪያ ኣድርገዋታል። ሁሌም ገዢ እንጂ ሻጭ ያልሆነች ሃገር ኣድርገዋታል ። እንደዛ ኣድርጋቹህ ያዙልን የተባሉ ነው የሚመስለው።
ሌላኛው ምሳሌ፣
አንድ ሰው ወደ ኢትዮጵያ ጥሬ ገንዘብ ይዞ ቢገባ ህገ ወጥ የገንዘብ ሽግግር ነው ተብሎ ይወረሰበታል ። ወደ ሃገር ዉስጥ ገንዘብ ይዞ መግባት ግን ምንም ጉዳት የለዉም። ከ ኣገር ዉስጥ ገንዘብ ይዞ ቢወጣ ግን ጉዳት ኣለው ሊባል ይቻላል። ስለዚህ ወደ ሃገር ለሚገባ ጥሬ ገንዘብ የሚወሲድ ከሆነ ማነው ጥሬ ገንዘብ ይዞ ወደ ሃገር ቤት የሚገባ። ለዚህም ነው ያደጉ ሃገሮች ወደ ሃገራቸው በሚገባ ገንዘብ ምንም ኣተኩሮ ኣያደርጉም። ምክንያቱም ወደ ኣገራቸው ዉስጥ ያሚገባ ይጠቅማል እንጂ ጉዳት የለዉም። የኛ ንጥቂያ ይመስል፣ የያዘዉን ሁሉ ዉሰድበት የሚል አሰራር አስገብተው ሲነጥቁ ይዉላሉ።
እንደ ትዝብቴ ከሆነ የኣዉሮጳዊያን እድገት በ ጭንቅላት ልዩነት የመጣ ሳይሆን መተጣጠፍን በደንብ ስለሚጠቀሙበት ነው ። ኣገር የሚጠቅመዉን ነገር በማድረግ ህዝባቸውን ና ሃገራቸዉን ይጠቅማሉ፣ የሚጠቅም ነገር ላይ ህጋቸዉን በቀለጠፈ ሁኔታ ያስተካክላሉ።
መተጣተፍ ኣስፈላጊ ነገር መሆኑን ለማየት በደቡብ አፍሪካ ካየሁት ኣንድ የመተጣጠፍ ችሎታ ትንሽ የምትመስል ነገር ግን ብዙ ኣስተማሪ የሆነች ነገር ልበል።
በኢትዮጵያ ግድግዳዎች ኣጥሮች ላይ ተጽፎ ኣየዉ የነበረ ነገር እንዲህ ይላል፣ « በዚህ ቦታ ሽንት መሽናት በህግ የተከለከለ ነው ወይም በዚህ ኣከባቢ መሽናት በህግ ያስቀጣል የሚል ነበር » ይህ ነገር ቢኖርም ግን መፈክሩ ብዙም ዉጤት አላስገኘም ነበር። ሰዎች ወደ ዛው ቦታ ሄደው ይሸናሉ። ይህ አይነቱ ዓሰራር ዉጤት እንደሌለው የተገነዘቡት የደቡብ ኣፍሪካ ባለስልጣኖች ደግሞ ችግሩን የሚያቃልሉት በተለየ መልኩ ነበር። ይሄዉም ሽንት በብዛት በ ሚሸናበት ቦታ ኣጥር ወይም ግድግዳ ኣከባቢ ሽንት መሽናት በህግ የተከለከለ ነው ብለው ኣይጽፉም ። ነገር ግን ሽንት በብዛት በሚዘወተርበት ቦታ፣ ሽንት ቤት ኣስፈላጊ እንደሆነ ስለሚረዱ። ከመከልከል ይልቅ እንደ መፍቻ በዛ ኣከባቢ ሞባይል ሽንት ቤት ያስቀምጣሉ ። ስለዚህ ወደዛ ቦታ መጥተው የሚሸኑት ሰዎች ሽንታቸዉን ያለምንም ፍርሃት ወይም መቸገር በሽንት ቤቱ ዉስጥ እንዲሸኑ ይደረጋል ማለት ነው፣ በዚህም በ ኣከባቢው ለሚከሰተው ሽታ መጥፋት መልስ ይሆናል ማለት ነው። እንደዚህ የመጠታጠፍና ነገሮችን በተለየ መልኩ በማየት ዉጤት ማምጣት ይቻላል።
መፍትሄ ለማምጣት የኣስተሳሰብ መተጣጠፍን ይጠይቃል።
Check online importation tax to Ethiopia here ( የማስገቢያ ቀረጥዎን በዚህ ሰንጠረጅ ማስላት ይችላሉ )
የባለሙያተኞች ደሞዝ ኣከፋፈል ስረዓቱን ማሻሻል
በተጨማሪ ኢትዮጵያ ከህልሟ ባንና ለ ባለሙያተኛ በአለም ደረጃ የሚከፈለዉን ደሞዝ መክፈል ካልጀመረች፣ ዜጎችዋን ኣስተምራ ለሌሎች ሃገሮች መገበሩዋን ከቀጠለች ድህነቷ ይቀጥላል። በአለም ደረጃ የሚከፈለዉን ክፍያ የሚያገኝ ሙያተኛ የሚያስፈልገዉን ሁሉ ማሙዋላት ስለሚችል ተወዳዳሪ ይሆናል፣ ሃግሩንም ያሳድጋል። ሃገር ለቆ መሸሹንም ይተዋል። የሃገር ተስፋም ይሆናል። ሞባይል ፎን መግዛት የማይችል ዶክተር ወይም እንጂነር እንዴት ሃገር ዉስጥ ሊቀመጥ ይችላል። ይሄ በሌሎች ሃገሮች ትንሽ የሚባለው ባለሙያተኛ እንኩዋን በቀላሉ መግዛት የሚችለው ነገር ነው።
እንድ ሃኪም ከ ኣማዞን ድረገፅ 10 ዶልላር የሚሽጥ መጽሃፍ መግዛት ካልቻለ ለምን ኢትዮጵያ ዉስጥ ይሰራል።እንዴትስ ሙያዉን ማዳበር ይቻለዋል። ፖለቲከኞች የፈለጉትን እያደረጉ፣ እሱ በተማረ ለሃገሩ ላገልግል ባለ ለምን በድህነት ይኖራል።
ይህ እስካሁን ባለመደረጉ፣ በሃገሪቱ ዉስጥ ያለዉን ችግር መቅረፍ ኣልተቻለም፤ በዚህ መልኩ ስንመለከተው እዉነት ኢትዮጵያን የሚያስተዳድረው መንግስት ኢትዮጵያዊ ይሆን ያስብላል። በእጅ ኣዙር በሌሎች ሃገሮች የሚተዳደር መንግስት ብቻ ነው የሃገሪቱን እና የህዝቦችዋን ማደግ የሚያስፈራው። በ ኒዎ ኮሎኒያሊዝም መሰሪ ኣሰራር ኣለም ኣቀፍ ድርጅቶች ሆን ብለው በሚጭኑት ጫና ሃገር የምትመራ ከሆነ ፣ የሃገር እድገት የማይታሰብ ነው። ምነው ኢትዮጵያ ከ ደቡብ ኣፍሪቃ መማር ሳትችል ቀረች ያስብላል።
ኢትዮጵያ በደርግ መንግስት ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ሃኪሞችን ኣፍርታለች፣ ቢሆንም ግን በሽተኞች እስካሁን ወደ ሲንጋፖር፣ ወደ ደቡብ ኣፍሪካ፣ ወደ ሌሎች ሃገሮች ሄደው ይታከማሉ። በሽተኛ ሃገር ዉስጥ መታከምና መዳን ካልቻለ፣ ታዲያ ሃኪም ማፍራቱ ለምን አስፈለገ ፣ በኢትዮጵያ የሰለጠኑ ሃኪሞች በተለያዩ የአፍሪካ ሃገሮች ወይም በሌሎች ያደጉ ሃገሮች ተቀጥረው እያገለግላሉ ይገኛሉ ። እነዚህ ሃኪሞች ሃገራቸውን ጠልተው ነው በሌላ ሃገር ሄደው የሚሰሩት፣ ወይስ ባለሙያ የሚገባዉን ክፍያ ባለማግኘቱ ነው።
ባለሙያን በሚገባ ሳይዙ እድገት ይመጣል ብሎ ማሰብ የደካሞች ነው። ይገርማል፣ የቀለለዉን ማሰብ ወይም መፍታት ያልቻለ መንግስት እንዴት ሃገሪቱዋን ወደ ፊተኛው ያሻግራታል።
የተማረ ሰው የሃገር እንቁ ኣይደለምን ፣ ታዲያ ባለሙያተኛ ሃገሪቱ ካላት ሌሎች ተፈጥሮዋዊ ሃብቶች ከሚባሉት
በምን ይለያል።ሁሉም የሃገር ሃብት ነው። እንቁ ና ወርቅ የተፈጥሮ ሃብታችን ነው ብለን ኣይደለም የምንጠብቃቸው ። የሰውም ሃይል የሃገር ሃብት ኣደለም እንዴ ጎበዝ።
የሚገርመው ይህንን ማሰብ ያልቻለ የሃገር ተቆርቁዋሪ፣ ኣስተዳዳሪና ፖለቲከኛ መኖሩ ነው። ለነገሩ በብዙ ኣመታት
የሙያ ስልጠና ወስዶ በ ዶክትሬት መዓረግ የተመረቀው ባለሙያ ፣ ሃይስኩል እንኩዋን በቅጡ ባልጨረሰ ፖለቲከኛ የሚመራበት ሃገር ዉስጥ እንዴት ባለሙያ እንደ ሃገር ሃብት ሊቆጠር ይችላል፣
በሰለጠኑ ሃገራት ባለሙያዉያን ለ ሚመጣው 50 አመት ለ 100 ኣመት ሁኔታዎችን አጥንተው ለህብረተሰቡ ምላሽ በሚሰጥ መንገድ ይሰራሉ። ለምሳሌ ከ 20 ኣመት በሁዋላ የህዝብ ቁጥር ስንት እንደሚሆን በመተንበይ ። የዉሃ ፣ የቤት ችግር፣ የ መሠረተ ልማት ፕሮጀችቶን ይሰራሉ ፣ የመሬት መጣበብ እንዳይኖር ኣስቀድመው ይዘጋጃሉ። ጊዜው ሲደርስም ህዝቡ ያለችግር ኑሮዉን እንዲያካሂድ ይረዳል ። ይህንን ለማድረግ የተከበረና በደንብ የሚከፍለው ባለሙያ ሊኖር ያስፈልጋል፣ ባለሙያ በጥሩ ሁኔታ ከተያዘ ደሞ እራሱን ለሙያው በመስጠት እንዲመራመርና ለህብረተሰቡ ችግር እንዲፈታ ይገፋፋል። ባለሙያ እየራበው ፣ የሚያስፈልገዉን ነገር መግዛት እየተሳነው እንዴት ለ ሚመጣው 30 እና 40 መት ማሰብ ይችላል። ኣይችልም
በኣሁን ሰዓት በሃገር ዉስጥ የሚታየው የተለያየ ችግር ሊከሰት የቻለው እንደዚህ ኣይነት ጥናት ባለመደረጉና፣ መንግስት ላለው ችግር መልስ መስጠት ባለመቻሉ ነው ። መንግስት መዘጋጀት ነበረበት። ጥናት ማድረግ ነበረበት። የስራ አጥነት መብዛ፣ ረሃብ፣ የወንጀል በከተማው መብዛት። የቤት ችግር መኖር። ከ 20 አመት በፊት ጥናት ተደርጎ ችግሩን ለመፍታት ኣስቀድሞ መዘጋጀትን ይጠይቃል። ሃገር ለንደዚህ ለመሳሰሉ ነገሮች አስቀድሞ መዘጋጀት እንዲችል ሙያተኞችን በደንብ መያዝ ያስፈልጋታል።
ኪንግ