ብዙ ሰዎች የትግራይ እና የኤርትራ ህዝቦች አንድ ናቸው ሲሉ እሰማለሁና እስኪ አንድነታቸዉንና ልዩነታቸዉን በጥቂቱ እንደሚከተለው እንመልከት
መቸስ ህዝብን በአንድ ባስኬት ዉስጥ ደምሮ ማየቱ ስህተት ቢኖረዉም ። በጠቅላላዉ ስንመለከተው ግን በነዚህ ህዝቦች ግንኙነት መካከል ስህተት ተሰርቶ እንደነበር ግልፅ ነው። የኤርትራ ህዝብ ደሞ በተለያየ ግዜ በትግራይ ህዝብ የተበደለ ህዝብ ነው። ስለዚህ ኤርትራዊያን የትግራይን ሰው በአይነ ቁራኛ ነው የሚያዩት ቢባል እንኳን ክፋት የለዉም ፤ ከታሪክ እና ከልምድ እንደምንማረው፤ በቁራኛ ማየታቸውን እንደ ጥንቃቄ ወይም እራስን እንደ መከላከያ ዘዴ ተደርጎ ቢታይ እንጂ ፤ እንደ ጥላቻ መታየት አይኖርበትም ። ያው ህዝብ ህዝብን ስለማይጠላ።
እስኪ በቋንቋ እንጀምር
የትግራይ ና የ ኤርትራ ህዝብ ተመሳሳይ ቋንቋ ይናገራሉ የሚለውን አባባል በምሳሌ እንመልከት ።
በትግራይ ትግሪኛ አሁን ማለት « ሕዚ » ሲሆን በ ኤርትራው ደግሞ « ሕጂ » ነው
ብትግራይ ትግሪኛ ዉሃ ማለት « ዉሃ » ነው በ ኤርትራው ደግሞ « ማይ » ነው። ርሁቅ ለማለት ደሞ ሊዩ ይላሉ
ስለዚህ አንድ የኤርትራ ተወላጅ በትግራይ ኖሮ የማያዉቅ ሰው የትግራይን ትግሪኛ ሊሰማ አይቻለዉም ። ስለዚህ እነዚህ ሰዎች በቁዋንቋ አይገናኙም ማለት ነው።
እንደትዝብቴ ከሆነ የትግራይ ሰዎች ወደ ኤርትራ ሲመጡ በትግሪኛ ሳይሆን የሚግባቡት በ አማርኛ ነው። ወይም ደሞ ኤርትራ ዉስጥ ቆይተው የኤርትራን ትግሪኛ ተለማምደው ነው የሚግባቡት እንጂ እንደሄዱ መግባባት አይችሉም። ሊሰማቸው የሚችል ሰው የለም። በተለይ የደቡብ ትግራይ ትግሪኛ ከሆነ።
በህብረተሰቡ ዉስጥ የሚታዩ ነገሮች
ለምሳሌ በኤርትራ ዉስጥ አጋሜ ማለት በጣም ክብር የሌለው ፤ ቫልዩ የሌለው እንደማለት ተብሎ ሊወሰድ ይቻላል ወይም ከዳተኛ እንደማለት ነው። እንዳስቀመጡት የማይገኝ ሰው ማለትም ሊሆን ይችላል።
በአንድ ወቅት በአስመራ ከተማ በአንድ ሻይ ቤት ሻሂ እየጠጣሁ በረንዳው ላይ ቁጭ ብዬ ሳለሁ። አንዲት ሴት ሌላኛዋን ሴት የአጋሜ ሚስት ብላ ስትሰድባት ሰማሁ ። ይህ ስድብ በጣም አፀያፊ ስድብ መሆኑን ያወኩት ፤ የተሰደበችዋ ሴት በጣም ተናዳ ተሳዳቢዋን እየጮኸች መታቻትና የቀለጠ ድብድብ ተጀመረ። የአጋሜ ሚስት የሚለው ስድብ እንዴት አሳፋሪ መሆኑን በዛን ግዜ ነው የተገነዘብኩት።
ለአንድ ኤርትራዊት እንደምርጫ አንድ አጋሜ ና አንድ አባጨጓሬ ቢቀርብላት በደስታ አባጨጓሬዉን ትመርጣለች ቢባል ማጋነነ አይሆንም። ስለዚህ የትግራይ ህዝብና የኤርትራ ህዝብ አንድ ናቸው የሚባለው ነገር ከየት እንደመነጨ አልገባኝም። እንደዉም የኤርትራ ህዝብ ከትግራይ ህዝብ ይልቅ ከጎንደር ህዝብ ጋር የተቀራረበ ባህሪይ አለው ሲባል ሰምቻለሁ።
ይህ የሚያሳየው ኤርትራዊያን በልባቸው ዉስጥ የትግራይ ሰው እንደሌለ ነው ። ይህ ማለት ኤርትራዊያን የትግራይ ሰው ይንቃሉ ማለት ሳይሆን ፤ በተለያየ ግዜ የትግራይ ሰዎች ኤርትራዊያንን በመዋሸትና በማታለል ብዙህ መከራና ግፍ እንዲወርድባቸው ያደረጉ በመሆናቸው ነው። የ 1998ቱ ጦርነት፤ ወያኔ በዉሸት ኢትዮጵያዉያንን አስተባብሮ ሻቢያን ለማጥፋት የተጠቀመበት ነበር። በሃይለስላሴም ጊዜ ተመሳሳይ ድርጊት አድርገዋል፣ በደርግ ጊዜም የደርግ ሰላይ በመሆን፤ በኢትዮጵያ ዉስጥም፤ በኤርትራ ዉስጥም ኤርትራዊያንን አስገድለዋል። በነ አሉላ አባ ነጋ ግዜም በማታለል የኤርትራዊያንን አገረ ገዢ ገድለዋል አስገድለዋል። ብዙ በደል በኤርትራዊያኖች ላይ አድርሰዋል። በ 1998 ደሞ ኤርትራዊያንን ከኢትዮጵያ አባረዋል። ከዚህ የተነሳ ኤርትራዊያን ትግራዮችን በአይነ ቁራኛ ማየት መጀመራቸው የሚያስደንቅ ነገር አይሆንም።
በነገራችን ላይ በኤርትራ ዉስጥ በሰላም ተከብረው የሚኖሩ የ ናይጀሪያ ኮሙኒትይ አሉ። በከረን አከባቢና ፣ ጥቂት በ አስመራ አከባቢ አርሶ አደር ሆነው ወይም ነጋዴ ሆነው ኑሮዋቸዉን ያስተዳድራሉ ። እነኚህ ሰዎች ወደ ኤርትራ የመጡበት ምክንያት ከ ናይጀሪያ ወደ ሶኡዲ አራቢያ (ወደ መካ ከተማ) በእግር ሲጓዙ ደክሞዋቸው በኤርትራ ዉስጥ አርፈው በዛው ኑሮዋቸዉን እንደቀጠሉ ይነገራል። ቁዋንቋዋቸዉም የናይጀሪያ ቁዋንቋዋ ነው። ስለዚህ የኤርትራ ህዝብ ሰው የሚጠላ ህዝብ አይደለም። ያከበረዉን አክብሮ የሚያኖር ትልቅ ህዝብ ነው። ፍቅርም አለው።
ሌላው ደሞ በሸአቢያ ሰራዊት ውስጥ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ከተለያየ ብሄረሰብ የተዉጣጡ የቀድሞው የደርግ ሰራዊት አባል የነበሩ በሻቢያ ተማርከው በኋላም በምርጫቸው ታጋዮች ሆነው ከኤርትራ ህዝብ ጋር አብረን እንታገላለን ብለው ጊዜያቸውን እና እድሚያቸውን ከሻቢያ ጋር ያሳለፉ እስካሁን ድረስ በኤርትራ ዉስጥ አሉ። ይሄ በጣም የሚገርም ሆኖ ነው ያገኘሁት ። እኔም በግሌ የሲዳማ ተወላጅ የሆነ ታጋይ በሰገነይቲ ከተማ አግኝቼ ስለህይወቱ ና እንዴት የሻአቢያ ታጋይ እንደሆነ ብዙ አጫዉቶኛል።
በመቀሌ ከተማ ከታዘብኩት
ባንድ ወቅት ፤ መቀሌ ዉስጥ የመሎቲ ቢራ 2.50 ብር ይሸጥ በነበረበት ግዜ ፤ ዋጋው ዝቅ ስለሚል ሰው ከሌላው ቢራ ይመርጠው ነበር ማለት ያቻላል ። የቡና ቤት ባለቤቶች እንዳስረዱኝ ከሆነ ግን ፤ የመቀሌ ከተማ ባለስልጣናት የመሎቲን ቢራ በፍሪጅ ዉስጥ እንዳያስቀምጡት ያዙዋቸው እንደነበረ ነው ። ምክንያቱም ፍሪጅ ዉስጥ ያልገባ ቢራ እራስ ምታት ስለሚያመጣ፤ ይህን በማሰብ የሚጠጣው ሰው እንዳያገኝ ወይም እንዳይሸጥ ሆን ተብሎ የሚደረግ ሴራ ነበረ ።
ሌላው ትዝብቴ ደሞ ፤ በአንድ ወቅት በቡና ቤት ዉስጥ ፤ አንድ ሰው እኛን ባየ ግዜ ፤ 10 መሎቲና አንድ ባልዲ አዝዞ፤ ከዛም ቢራዎቹን በባልዲ ዉስጥ አፈሰሰና እንዲህ ሲል ተናገረ « መሎቲ ቢራ ሰው አይጠጣዉም፤ የባልዲ ማጠቢያ ነው አለ » ። በተጨማሪም ሌላ ተመሳሳይ ነገሮች መቀሌ ዉስጥ ታዝቤያለሁ።
ሸአቢያ ወያኔን ለምን ይረዳው ነበረ?
ሸአቢያ ወያኔን ይረዳው የነበረው ስለሚወደው ወይም የትግሬ ዉድብ ስለሆነ ሳይሆን ደርግን ለማዉደቅ ስትራቴጂካዊ ና ፖለቲካዊ ጥቅም ስለነበረው ብቻ ነው።
በ 1972 አመተ ምህረት አከባቢ ሸእአቢያ ና ሌሎች አጋር የነፃነት ተዋጊ ሃይሎች የኤርትራን ምድር ተቆጣጥረዉት እንደነበር ና አስመራ አከባቢን ይዘውት እንደነበር ይነገራል፤ ይህም ማለት ደርግ የተሸነፈው በዚሁ ግዜ ነበር ማለት ነው ፤ ቢሆንም ሸአቢያ ደርግ ሳይወድቅ ኤርትራን ነፃ ካወጣን፤ ደርግ በቦንም ህዝብ ሊጨርስ እንደሚችል ስለታሰበ ፤ እንደገና የተቆጣጠሩትን ቦታዎች በመተው ወደ ናቅፋ ተመለሱ ፤ ከዛም ወያኔን እና ሊሎች ዉድቦችን በማቁዋቋም ደርግን ለመጣል እንደገና መስራት ጀመሩ ማለት ነው። ስለዚህ ወያኔ ለስትራቴጂካዊ ጥቅም ሲባል የተደራጀና የታገዘ ድርጅት እንጂ፤ የትግሬ ድርጅት ስለሆነ የታገዘ አልነበረም። በዘር ላይ የተመረኮዘ መረዳዳት አልነበረም ለማለት ነው። ለነገሩ ሸአቢያ ኦነግንም ረድቶዋል ፤እስከቅርብ ጊዜም ድረስ ሲያግዘው ቆይቶዋል ።
ወያኔ በኤርትራ ዉስጥ ገብቶ እንዳይገለኝ ያለ ኢትዮጵያዊ ዲያስፓራ ጎብኚ እንዳለ ሰምቻለሁ
መልእክቴ እንደሚከተለው ነው
ወያኔ እንዃዋን ኤርትራ ዉስጥ ገብቶ ሰው ሊገል ፤ በአሁኑ ሰአት እዛው ባሉበት በፍርሃት እየኖሩ እንደሆነ የሚያጠራጥር ነገር የለዉም ። የ 1998 ጦርነት መከፈቱ፤ የወያኔን ፍራቻ የሚያሳይ እንጂ ጀግንነቱን ወይም ጉልበቱን የሚያሳይም አልነበረም ። ስለዚህ ወያኔ ኤርትራ ዉስጥ ገብቶ የመግደል አቅም የለዉም። በተጨማሪም የሻቢያ ሴኩሪቲ እንደ ሸረሪት ድር በመሆኑ፤ የወያኔ አሳሲን ኤርትራ ገብቶ የመግደል ሙከራ ማድረግ የማይታለም ነው።
ወያኔ አቅም እንደሌለው የሚታወቀው ደሞ
ጦርነት ከሻቢያ ጋር ማድረጉ ስትራቴጂካዊም ይሁን ፖለቲካዊ ጠቀሜታ እንደሌለው አስቀድመው ባለማወቃቸው ፤ ይሄንን ደሞ መረዳት ስላልቻሉ ዉጊያ በኤርትራዊያን ላይ መክፈታቸው ። የወያኔ መሪዎች ብቃት እንደሌላቸው ያስመሰከሩበት ጦርነት ነበረ ። ብልጥ መሪ ቢሆኑ ኖሮ ከኤርትራ ጋር ዉጊያ መጀመር እንደማያዋጣና ጥቅምም እንደሌለው ከወዲሁ መገመት መቻል ነበረባቸው ። ለዛም ነው ጦርነቱ ያልተሳካው። የአሳስተሳሰብ አቅም ቢኖራቸው ኖሮ ፤ በኢኮኖሚ እንዴት አብሮ ማደግ እንዳለባቸው በመተባበር ለመስራት ይተጉ ነበረ።
ወያኔ አላማዋ የነበረው ፤ ሸአቢያን ስለምትፈራ ፤ የኢትዮጵያን ሰራዊት አስተባብራ ሸአቢያን ለማጥፋት እና የ አከባቢው ጎብለል ተብሎ ተፈርቶና ተከብሮ ለመኖር የተደረገ ሙከራ ነበረ ።
የ ESAT TV አስተያየት
ጦርነት ምን እንደሚመስል የማያዉቁ ሰዎች አስተያየት በ ESAT TV መስኮት ሲያወሩ እንደሰማሁት፣ ኢትዮዮጵያ ብትፈልግ ኖሮ ኤርትራን መደምሰስ ትችል ነበረ ሲሉ ሰምቻለሁ።ይሄ አስተሳሰብ ጦርነትን ካለማወቅ የመነጨ አስተሳሰብ ነው። ወይም በእውቀት ያልተደገፈ እስተያየት ነው ሊባል ይቻላል።
ኢትዮጵያ የሚቻላትን ሁሉ አድርጋ ነበር። ጦርነቱን ለማሸነፍ ግን አልቻለችም ። በመጨረሻው ሰአት በአልጀርስ ፊርማ ከተፈረመ በሁዋል እንኳን ፣ በትንሹም ቢሆን አሰብን እንኳን እንያዝ ተብሎ ለ 11 ቀን ሙሉ በአከታታይ በ አየርና በ የብስ በቡሬ ግንባር አሰብን ለመቆጣጠር በተደረገው ርብርቦሽ ወያኔ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰራዊቱን በጥቂት ሰአታት ያጣበት አሳዛኝ ዉጊያ እንኳን በድል አልተጠናቀቀም። የኤርትራ ሰራዊት እንደዝናብ ይወርድበት የነበረዉን ቦንብ በፅናት የመከተበት ግዜ ነበር። ይሄ ደሞ ጦርነት በህዝብ ብዛት ወይም በወታደር ብዛት አሸናፊነት እንደማይገኝ የሚያሳይ ምሳሌ ነው።
ወያኔ እግሩ ስላበጠ የጎለበተ መስሎት ነበረ ። ቢሆንም በድል ለመጨረስ ስላልቻለ ጦርነቱ ቆሞዋል። እንዲያዉም በተገላቢጦሽ ጦርነቱ ቀጥሎ ቢሆን ኖሮ ለኢትዮጵያ በጣም አስጊና አደገኛ ይሆን እንደነበር የሚያጠራጥር አልነበረም።
በሌላ ወገን ደሞ ፤ የኢትዮጵያ ሰራዊት ወደ ባረንቱ ድረስ ዘልቆ የገባበት ምክንያት፤ የጦርነት እስትራቴጂ ስለሆነ ነው እንጂ ወያኔ አሸናፊ ስለነበረምን አደለም። የኤርትራ ሰራዊት ቦታ ለቆ ወደ ሁዋላ ማፈግፈጉ በደንብ ከቦ በቀላሉ ማጥቃት እንዲቻለው የተደረገ ወታደራዊ ስልት እንጂ ፤ወያኔ ስለበረታም አይደለም ። ጦርነት ላይ ሳይዉሉ ስለጦርነት አስተያየት መስጠት አለማወቅን ያሳያል እንጂ ተሰሚነትን አያስገኝም ።
በሌላ በኩል ደሞ ጦርነት መሪ ያስፈልገዋል። መቼስ መለስ በጦር ሜዳ ሆኖ ሰራዊት ሲያዝ ነበር ሲባል አልሰማሁም። ኢሳያስ ግን በጦርነት ውስጥ ሆኖ ጦርነቱን ሲመራ ፤ ሲያስተዳድር በአይኔ በብረቱዋ አይቸዋለሁ።
በአከባቢው ሆኜ ጦርነቱን በቅርብ እከታተል ስለነበረ ወይም የጦርነቱ ተሳታፊ ስለንበርኩ እና ዉጊያዉን ብግብር ስላየሁት እዉነቱ ከዚህ የተለየ ነው የሚል እምነት የለኝም ።
ለማጠቃለል
ታዲያ እነኚህ ህብረተሰቦች ግንኙነታቸው በምን እንደሆነ ግልፅ አይደለም ። በቁዋንቋ አይገናኙም፤ ባህሪያቶቻቸው በ ፖላሪትይ እንኳን ቢታይ በ ፖዘቲቭ እና በኔጋቲቭ ፖል ያሉ ናቸው ፤ የተለያየ ፖላሪትይ ያላቸው ህብረተሰቦች ናቸው ማለት ነው፤ አርምባና ቆቦ ናቸው ቢባል ትክክል ነው። ፤ ታዲያ ተመሳሳይነታቸው እንዴት ነው ቢባል ሁለቱም በሰሜን ኢትዮጵያ መኖራቸው ብቻ ይሆናል መልሱ።
የትግራይ ህዝብና የኤርትራ ህዝብ ጥሩ ግንኙነት ሊኖር የሚችለው ባለፈው ታሪክ ሳይሆን ከእንግዲ ወዲህ በሚኖረው የበሰለና የአርቆ የማሰብ ስልጡን አስተሳሰብ ላይ በተመረኮዘ ዝምድና ነው የሚሆነው። ድሮ አልነበረም ማለት ይቻላል ።
King
Asmara, Eritrea through American eyes