በአሁኑ ወቅት በኤርትራ ዉስጥ እንደሚታየው ኢሰያስ የተለያዩ ድራማዎች እየሰራ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ለምሳሌ በባዶ 3 (03) እየተሰራጩ ያሉት ወሬዎች ሆን ተብሎ ለማደናገሪያ የሚሰደዱ ወሬዎች መሆናቸው አያጠራጥርም ፤ ኢሰያስ ኢትዮጵያን በታትኖ እንደገና ለመስራት ለሚያደርገው ሴራ የተለያዩ መሸፈኛ ( camouflage) ድራማዎች እየሰራ ይገኛል፡፡ ያው እንደምናዉቀው ኢሰያስ ስልጣኑን ለማራዘም የተለያዩ ስልቶችን እየነደፈ የሚንቀሳቀስ alligator ነው፣ a homegrown alligator.
ባለፈው ሳምንት ዉስጥ ካየናቸው ክስተቶች ብዙዎቹ assignment ስለመሆናቸው ኢሱን ለሚያዉቅ ድንግር አይለዉም፡፡ ለምሳሌ የአብርሃም ኢሰያስ ወደ ስልጣን እንደመጣ አስመስሎ በ TV ሆነ ተብሎ መሰራጨቱ፣ ብዙ ኤርትራዊያን ወደ ኢትዮጵያ ስደት መሄዳቸው ፣ ኢትዮጵያዊያን ነጋዴዎች ወደ ኤርትራ መጥተው invest እንዲያደርጉ እየተፈቀደላቸው ነው የሚባለው ወሬ ትክክል ቢሆንም እንኳዋን ፣ ዋናው አላማው ግን ማደናገሪያ ና አቅጣጫ ማስቀየሪያ ነው ፡፡
በኤርትራዊያን በኩል የኤርትራን ወደብ ለኢትዮጵያ አስረከበ፣ ሉአላዊነታችንን ስጋት ላይ አወደቀው የሚሉ ፍርሃቶች በግልፅ ይታያሉ፡፡ legitimate fear ነው፡፡ ነገር ግን የኤርትራ ሉአላዊነት ስጋት ላይ ከወደቀ፣ የኢሳያስን ስልጣን ስጋት ላይ ስለሚጥል ይሄ ይሆናል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡ be cool Eritreans! no worries!
የኢሳያስን ያለፉ ስራዎችን ብንመረምር የወቅቱ ሴራ አቅጣጫው ወዴት እንደሚያመለክት መገመት አያቅትም ፡፡ ኢሱ ሃሳቡን ለማሳካት ግማሽ ኤርትራን እንኳን ሰጥቶ ከሚፈልገው ቦታ ለመድረስ ወደሁዋላ የማይል ሰው መሆኑን ከልምድ አዉቀናል፡፡ መሬት ወይም ወደብ የትም እንደማይሄድ ያዉቃል ፡፡ በተለይ ኢትዮጵያ ከተተራመሰች በሁዋላ እንደሚመለስ ያዉቃል፡፡ ባይመለስ እንኳዋን መጨረሻ ላይ ህልሙ ሲሳካ፣ ሁሉም ተመልሶ የራሱ እንደሚሆን ያዉቃል፡፡ በአሁኑ ወቅት ኢሱ አደገኛ ቁማር እየተጫወተ መሆኑ ግልፅ ነው፡፡ ኢትዮጵያን አፈራርሶ እንደገና በራሱ አደረጃጀት ለመገንባት ድንጋይ እየፈነቀለ ይገኛል፡፡ ዋናው አላማው ለራሱ ስልጣን ማጎናፀፍና፣ እራሱ ከካደው ህዝብ መከላከል ሆኖ ፣ በአጀንዳነት ግን ታላቂቱዋን ምስራቃዊት አፍሪካ ዳግም መመስረት በሚል አጀንዳ የዋህ አጋሮቹን ሞቢላይዝ በማድረግ ለኢትዮጵያ ተቆርቋሪ መስሎ በሚስጥር ማፈረካከስና በመቀጠልም እንደገና ለራሱ እንደሚመቸው አድርጎ መገጣጠም ነው፡፡
ባለፈው ሁለት ሳምንታት እንደታዘብነው፣ ኤርትራዊያን ወደ ኢትዮጵያ ስደት መሄዳቸው ኢሰያስን ዳንኬራ የሚያስረግጥ ነገር ነበር ማለት ይቻላል፡፡ ምክንያቱም ድንበር በመከፈቱ ከስደተኛ ጋር ቀላቅሎ የስለያ አባላቱን በብዛት ወደ ኢትዮጵያ ሰርገው እንዲገቡ ማድረግ ስለሚያስችለው፡፡ ይህም ሆነ ተብሎ የሚደረግ ደባ ነው፡፡ ኢትዮጵያን ከዉስጥ ለማፍረስ ሃይለኛ ተንኮል እንዳለ ማወቅ ያስፈልጋል፡፡
የወቅቱን ሁኔታ ተጠቅሞ ፣ የርስ በርስ ግጭቱን ማባባስ እና ኢትዮጵያ ኮላፕስ እንድታደርግ ማመቻቸቱ የወቅቱ አጣዳፊ ጉዳይ ነው፡፡ የኢሰያስ ህልሙ ባይሳካለትም እንኳዋን ማተራመስን እንደምርጫው አድርጎ እራሱን ስልጣን ላይ ለማቆየት የማይፈነቅለው ድንጋይ የለም ፡፡ for him, this is the only way to survive፡
በኢትዮጵያ በኩል ደሞ፣ የቆጡን አወርዳለሁ ብላ የብብቷዋን ጣለች እንደሚባለው፣ አይን አሰብ ና ምፅዋ ላይ ማድረጉን ትቶ ዋናዉ ነገር ላይ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡ ፈረንጆች እንደሚሉት Eye on the Prize!
የወደፊቱን ክስተቶች ከወቅታዊ ሁኔታዎች በማዛመድ አቅጣጫ ማመላከት ጥሩ ቢሆንም፡ እርግጠኛነቱ ግን በጊዜ የሚታይ ነው፡፡ ስለዚህ ጊዜ እራሱ እየተፈፀመ ያለዉን ድርጊት እስኪፈታው ወይም ትክክለኛ አቅጣጫ እስኪያሳየን በትግስትና በተጠንቀቅ መጠበቅ ያስፈልጋል፡፡
ኪንግ