የቴክኒክ ሙያ ብዙ ልምምድና ተግባራዊ ስልጠና የሚጠይቅ፣ እልህ ኣስጨራሽ ሙያ ነው። ጊዜ ወስዶ ፣ ታጋሽነትን ጨምሮ ብዙ ምርምርና ወጪዎችን ከፍሎ የሚደረስ የሙያ ዘርፍ በመሆኑ ብዙ ጽናት ና ቁርጠኝነትን (dedication) ይጠይቃል፣ ስለዚህም ነው ጥቂቶች ብቻ በዚህ ሙያ ሰልጥነው ና ተመርቀው ኣገልግሎት ለመስጠት ብቁ ሆነው በሙያው የሚሰማሩት።
በተለይ በዚህ በቴክኖሎጂ ዘመን ፣ የፈጠራ ስራ በፍጥነት በሚለዋወጥበት ሁኔታ ፣ ሙያው በየጊዜው እውቀትን ማዘመን ስለሚጠይቅ ፣ የስራዉን ኣስቸጋሪነት በበለጠ ያከብደዋል። ስለዚህ በዘርፉ የተሰማሩትን ሙያተኞች መደገፍና ማበረታታት በዚህ ዘርፍ ሊከሰት የሚችለዉን የኣገልግሎት ክፍተት በእጅጉ ለማስወገድና የተቀላጠፈ ዘመናዊ ኣገልግሎት ለመስጠት ያስችላል።
ወጣት ሙያተኞችን በብዛት ለማፍራት እንዲቻል፣ ባደጉት ሃገሮች እንደሚደረገው ፣ በተለያዩ የቴሌቪዥን አስተማሪ ስርጭቶችን በማስተላለፍ የወጣቱን ፍላጎት በመቀስቀስና ድጎማዎችን በማድረግ ሙያዊ ተሳታፊነትን ለማብዛት መስራትን ይጠይቃል። በዉጭ ሃገር ያሉ የቴሌቪዥን ስርጭቶች ከብዙው በጥቂቱ እንደ ምሳሌ ለመጥቀስ፣ እንደ ፣ ፒምፕ ማይ ራይድ (Pimp my ride)፣ ዊለር ዲለር (wheeler dealer) ፣ ኪንደኢግ ኢት ከስተም (kindig it custom) የሚባሉ የቴሌዥን ስርጭቶች ለወጣቱ ህብረተሰብ ወደ ሙያው ዘርፍ እንዲመጣ የሚያደርጉት ኣስተዋጸኦ የላቀ ነው። በሃገር ዉስጥ፣ እንደነዚህ የመሳሰሉ ስርጭቶችን እንዲበዙ ማበረታቻ በማድረግ የወጣቱን ኣትኩሮት መሳብና ተሳታፊነትን ማብዛት፣ የቴክኒክ ሙያ ኣገልግሎትን ለማቀላጠፍና ለማሻሻል ያግዛል።
በተጨማሪም፣ ልምዱ ያላቸው መካኒኮች እዉቀታቸዉን ለሚቀጥለው ትዉልድ ማካፈል የሚያስችላቸዉን መድረክ ኣዘጋጅቶ በተለያየ መልኩ ተሳታፊነታቸዉን በማስፋትና ወጣቶችን እንዲያስተምሩ እድሉን መፍጠር ለወደፊቱ የባለሙያ እጥረትን ለመቀነስ ያግዛል።
ምሳሌያዊ የቴሌቪዥን አስተማሪ ስርጭቶች የሚከተሉትን ቪዲዮች ይመስላሉ፣
- ፒምፕ ማይ ራይድ (Pimp my ride)
- ዊለር ዲለር (wheeler-dealer)
- ኪንደኢግ ኢት ከስተም (Kindig it custom)
የድህረ ገጹ ኣስተዳዳሪ (webmaster)